የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪው ድጋፍ ያስፈልገዋል Featured

17 Apr 2018

 

አዲስ አበባ፦ የአገሪቱ የምግብና መጠጥ ዘርፍ ብዙ ያልተሠራበትና መደገፍ የሚገባው መሆኑን የምግብ መጠጥና ፋርማሲውቲካል ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ታደለ በተለይ ከጋዜጣው ሪፓርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ የምግብና የመጠጥ ኢንደስትሪው በአገሪቱ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ቢሆንም በኋላ ቀር ቴክኖሎጂና በትኩረት ማነስ ሳቢያ ምርታማና ተወዳዳሪ መሆን ተስኖታል።
ይህንን ሁኔታ በመቀየርና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዎችን በማሸጋገር ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋጋ፣ በብዛትና በጥራት ተወዳዳሪ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህን ማሳካት የሚቻለው የአምራቾች የዘወትር ጥያቄ የሆነውን ከአገር ውስጥም ከውጭም የሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች እጥረት በሚፈለገው ደረጃ ማሟላት ሲቻል መሆኑን አብራርተዋል።
አገሪቱ ካላት ተፈጥሯዊ ጸጋ አንጻር ዘርፉ ገና ምንም ያልተሠራበትና ትኩረት ማድረግን የሚሻ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህንን ሁኔታ በመቀየርና ዘመናዊ ቴክኖሎ ጂዎችን በማሸጋገር ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋጋ በብዛትና ጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ በተለይም የምርት ማሸጊያዎችን ጥራት ማስጠበቅ ላይ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በላብራቶሪ ፈትሾ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠትም እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የዱቄት ምርት በላብራቶሪ ተፈትሾ እንዲያልፍ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች እንዳሉ አብራርተው፣ ለምሳሌ የግልና የመንግሥት ላብራቶሪዎች ከዩኒቨ ርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር ጋር በመቀናጀት የቴክኖሎጂ ሽግግር እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።
በሌላ በኩልም በአገራችን በብዛት ከሚመረተው ጤፍ ሌሎች የምግብ ዓይነቶች እንዲዘጋጁ ለማድረግ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች እየተቀዱና ወደ ተግባር እየተቀየሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ምርቶቹን ወደ ውጭ መላክ መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡
«ቴክኖሎጂን ማፍለቅ ብዙ አቅምን የሚጠይቅ በመሆኑ አሁን እየተሠራ ያለው ከአደጉት አገሮች በመቅዳት ነው›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዚህም ቴክኖሎጂውን በማላመድ የማሸጋገር ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

እፀገነት አክሊሉ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

የጎብኝዎች ብዛት

0002829547
TodayToday1177
YesterdayYesterday1980
This_WeekThis_Week7267
This_MonthThis_Month29727
All_DaysAll_Days2829547

       በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።