የማዳበሪያ አጠቃቀሙ ምርታማነትን እያሳደገ ነው Featured

17 Apr 2018

 

አዲስ አበባ፡- በአፈር ምርመራ ውጤት ላይ የተመረኮዘው የማዳበሪያ አጠቃቀም ምርታማነትን ማሳደግ እያስቻለ መሆኑን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአፈር ለምነት ማሻሻያ የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ከፍተኛ ባለሙያው አቶ ፋኖሴ መኮንን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት፤ የአፈር ለምነትን በመጠበቅና የተጎዳ አፈርን አክሞ ወደ ምርታማነቱ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ በ 2004 ተጀምሯል፡፡ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከአፈሩ ይዘት ጋር የሚጣጣሙ የተለያዩ የማዳበሪያ ዓይነቶች የመጠቀምና የማስተዋወቅ ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ውህድ፣ ምጥን እና ፖታሽ ማዳበሪ ያዎች ለአርሶ አደሮች እየተሰራጩ መሆኑን ባለሙያው ጠቅሰው፣ በዚህም በአማራ ክልል በስንዴ ምርት ከ6 ኩንታል በላይ፣ በጤፍ ደግሞ ከ2 ኩንታል የሚበልጥ ብልጫ ያለው ምርት በሄክታር ማግኘት መቻሉን አመልክተዋል።
ባለሙያው እንዳመለከቱት፤ በኦሮሚያ ክልል አዳዲሶቹን የማዳበሪያ ዓይነቶች በመጠቀም በሄክታር ስንዴ ከ10 ኩንታል እንዲሁም ጤፍ በሄክታር ከ4 ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል።
«አፈር በባህርይው ተለዋዋጭ ነው» ያሉት አቶ ፋኖሴ፣ ይህ ምርታማነት እንደ የክልሎቹ ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እንደ ባለሙያው ማብራሪያ፤ ኢትዮሲስ በተባለ ፕሮጀክት አማካይነት ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ እንዲሁም ከሌሎች የምርምርና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በአፈር ናሙና ምርምር ውጤት ላይ የተመረኮዘ የማዳበሪያ አጠቃቀም ሥርዓት እየተከናወነ ነው።
በጥናቱ ወቅትም በየአካባቢው ምን ዓይነት አፈር እንዳለ በውስጡ የጎደሉ ነጥረ ነገሮችም የትኞቹ እንደሆኑ በመለየት የሚያስፈልገው ማዳበሪያ ይለያል፤ ከዚያም በሄክታር ምን ያህል መጠን ያስፈልጋል የሚለው ይሰራል።
አቶ ፋኖሴ እንደሚሉት፤ ለዚሁ ሥራ ታስቦ በአገር ውስጥ አምስት ያህል የምጥን ማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ተገን ብተው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ ባላቸው አቅምም የሚፈለግባቸውን እያመረቱ እንደ ሚገኙም ባለሙያው አመልክተዋል።

እጸገነት አክሊሉ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

የጎብኝዎች ብዛት

0002829551
TodayToday1181
YesterdayYesterday1980
This_WeekThis_Week7271
This_MonthThis_Month29731
All_DaysAll_Days2829551

       በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።